የሀገር ውስጥ ዜና

የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር አሶሳ ገቡ

By ዮሐንስ ደርበው

December 04, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ገብተዋል።

አፈ ጉባዔው አሶሳ ሕዳሴ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ በአሶሳ ማዕከል ለመንግሥት አመራሮች እየተሰጠ ባለው ሥልጠና ላይ ማጠቃላያ ይሠጣሉ መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!