የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ሐዋሳ ገቡ

By ዮሐንስ ደርበው

December 04, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተሠጠ ባለው አራተኛ ዙር የመንግሥት አመራሮች የዐቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ማጠቃለያ ለመስጠት ሐዋሳ ገብተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አወል ሐዋሳ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብረሃም ማርሻሎ እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ ተሰማ ዲማን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አቶ አወል በሐዋሳ ማዕከል “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተሠጠ ባለው 4ኛ ዙር የመንግሥት አመራሮች የዐቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ተገኝተው የዕለቱን ማጠቃለያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!