አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮፕ28 ጉባኤ ለጋሽ ሀገራት የሀሩራማ አካባቢ በሽታዎችን ለመከላከል 777 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
ቃል የተገባው ገንዘብ በፈረንጆቹ 2030 ሀሩራማ በሽታዎችን ለመከላከል በዓለም ጤና ድርጅት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ነው ተብሏል።
ገንዘቡ ችላ የተባሉ ሀሩራማ በሽታዎችን ለመቆጣጠር፣ ለመከላከልና ለማጥፋት እንደሚውል ተመላክቷል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚደረገውን ትግል አጠናክሮ ለመቀጠልና ሀሩራማ በሽታዎች ሥር የሰደደባቸው ሀገራትን ለመታደግ ለቀረበው አስቸኳይ ጥሪ ለጋሾች ምላሽ መስጠታቸው ተገልጿል።
ጥሪው በዓለም ዙሪያ ለሀሩራማ በሽታዎች ተጋላጭ የሆኑ ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት ለመታደግና ለማሻሻል በጋራ መስራትን ያነገበ መሆኑን የገልፍ ቱደይ ዘገባ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!