Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የባህል ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)18ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ “ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ የባህል ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው።

በባህል ፌስቲቫሉ ላይ ሁሉንም ብሔር፣ ብሔረሰቦች የሚወክሉ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን÷ የተለያዩ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የባህል ምግቦች፣ አልባሳት እና ባህላዊ ውዝዋዜዎች እያቀረቡ ነው።

በፌስቲቫሉ ላይ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የመዲናዋ ነዋሪዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ታዳሚዎች መገኘታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ “ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ህዳር 29 በጅግጅጋ ይከበራል።

Exit mobile version