የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በ “ብሪክስ” ሀገራት ስብሰባ እየተሳተፈች ነው

By ዮሐንስ ደርበው

December 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ ደርባን እየተካሄደ በሚገኘው የ ”ብሪክስ” ሀገራት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር ለመሆን የቀደመ የዲፕሎማሲ ልምዷ እንዳገዛት አስረድተዋል፡፡

ለአብነትም የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል መሆኗን ጠቅሰው የተመድ እና የአፍሪካ ኅብረት መሥራችነቷን አንስተዋል፡፡

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በታሪኳ በዲፕሎማሲ እንደምትታወቅ አስገንዝበው የብሪክስ አባል ለመሆንም ይሄው የካበተ የቀደመ ታሪክ ረድቷታል ማታቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ የ“ብሪክስ”አባል መሆኗም ከሀገራት ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማጠናከር ያለፈ ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ እንዳለው በአጽንኦትገልጸዋል፡፡

አባልመሆኗም ሉዓላዊነቷን ባከበረና በእኩልነት መርኅ ላይ የተመሠረተ ስትራቴጂያዊ የንግድ፣ የልማት፣ የኢንቨስትመንት እና የጋራ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ የሚያስችል ዕድል ይፈጥርላታል ነውያሉት፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የ”ብሪክስ” አባልነት ጥያቄውን ካቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ተቀባይነት እስከሚያገኝ ድረስ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱንም ነው አቶ ማሞ ያስታወሱት፡፡

የቡድኑ ትኩረት ፉክክክር ውስጥ መግባት ሳይሆን የደቡብ ቀጣና ሀገራት ትሥሥርና የጋራ ራዕይ እንዲቀጥል እንዲሁም የጋራ ብልፅግናቸው ዕውን እንዲሆን ማስቻል ነው ብለዋል፡፡

የ”ብሪክስ” አባል ሀገራት በቡድኑ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ፣ የባለ ብዙ ወገን ግንኙነቶችን በማጠናከር ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ እንዲሁም በዓለም ሠላም እና ብልፅግና ለማሥፈን እንዲሠሩ ጠይቀዋል፡፡

እንደ ቡድን በፈረንጆቹ 2024 ቅድሚያ ተሠጥቷቸው በሚሠሩ ጉዳዮች ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!