Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አርሰናል ዎልቭስን በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ዎልቭስን 2 ለ 1 በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት አጠናክሯል፡፡

ምሽት 12፡00 ላይ በተደረገው ጨዋታ ቡካዮ ሳካ እና ማርቲን ኦዲጋርድ የአርሰናልን ጎሎች ሲያስቆትሩ ማቲያስ ኩና የዎልቭስን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተክትሎም በውድድሩ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው የአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድን÷ ነጥቡን 33 በማድረስ የፕሪሚየርሊጉን መሪነት ማጠናከር ችሏል፡፡

በሌላ ጨዋታ ብሬንትፎርድ ሎተን ታውንን 3 ለ 1፣ በርንሌይ ሼፊልድ ዩናይትድን 5 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

 

Exit mobile version