አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ለሶማሊያ የጦር መሣሪያ እንዳይሸጥ ከ30 ዓመታት በፊት ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ ማንሳቱ ተገለጸ፡፡
ማዕቀቡ የተነሳው በትናንትናው ዕለት ምክር ቤቱ በድምፅ ብልጫ ባሳለፈው ውሳኔ መሆኑን አር ቲ ዘግቧል፡፡
በፈረንጆቹ 1992 ላይ በዚያድ ባሬ የሥልጣን ዘመን በሶማሊያ በተከሰተው አለመረጋጋት ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር መበራከቱን ተከትሎ ነበር ተመድ ማዕቀብ የጣለው፡፡
በዚህም በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የጦር አበጋዞች መብዛታቸውን ተከትሎ ሥጋት በመፈጠሩ እንቅስቃሴያቸውን ለመገደብ ማዕቀቡ ተጥሎ መቆየቱ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!