Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ለካርበን ልቀት ክፍያ እንዲከፈል ግፊት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን በዓለም ዙሪያ ሁሉም ለካርበን ልቀት እንዲከፍሉ ጥሪ አቅርበዋል።
 
በዓለም ዙሪያ 73 የካርበን ዋጋ መመዝገቢያ መሳሪያዎች እንዳሉ የጠቆሙት ፕሬዚዳንቷ÷ ነገር ግን ከዓለም አቀፍ ልቀቶች ውስጥ 23 በመቶውን ብቻ እንደሚሸፍኑና ይህ ድርሻ መጨመር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
 
ይህ ድርሻ ልቀት በፍጥነት እንዲቀንስ፣ ለዓለም አቀፍ ንግድ ምቹ ስነ ምህዳር ለመፍጠር እና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ጨምሮ ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት እርምጃ ተጨማሪ ገቢ እንደሚያስገኝም አመላክተዋል።
 
ቮን ዴር ሌይን አያይዘውም በዓለም ላለው የካርቦን ልቀት ዋጋ ማውጣት ላይ መሰራት አለበት ሲሉም ተናግረዋል፡፡
 
የካርቦን ዋጋ አወጣጥ ለበለጠ የግል ኢንቨስትመንት ፈጠራ አስተዋፅዖ እንደሚያደርግና ብክለት አድራሾች ፍትሃዊ ዋጋ እንዲከፍሉ በማድረግ ገቢው የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት አስተዋፅኦ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።
 
መልእክቱ ግልፅ እንደሆነ ያነሱት ፕሬዚዳንቷ÷አየር እየበከሉ ያሉ አካላት ዋጋ እንዲከፍሉና ክፍያውን ለማስቀረት ከፈለጉ ከካርቦን ነፃ የሆነ ፈጠራ እንዲፈጥሩ አሳስበዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version