በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክረው የኮፕ28 ጉባኤ በዛሬው ዕለት በዱባይ ተጀምሯል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክረው የኮፕ28 ጉባኤ በዛሬው ዕለት በዱባይ ተጀምሯል።
ጉባኤው በተለያዩ ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክርና ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም ይጠበቃል፡፡
በጉባኤው የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የዓለም ሙቀት ከ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ በታች እንዲሆን አስቸኳይ እርምጃ ያስፈልጋል ብለዋል።
የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመቆጣጠር መሪዎች ለወደፊት ከቅሬተ አካል ነዳጅ ውጭ ዕቅድ እንዲያወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የዓለም መሪዎች በዱባይ የሙቀት መጨመር እና ሁለት ዋና ዋና ጦርነቶችን በመቃወም ንግግር አድርገዋል።
የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲን የአስተዳደራቸው የማዕዘን ድንጋይ እንደሚያደርጉ ቃል በመግባት ባለፈው ዓመት ስልጣን የተረከቡት የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የአየር ንብረት ለውጥን “የሰው ልጅ እስካሁን ካጋጠመው ትልቁ ፈተና” ብለውታል።
ነገር ግን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተግዳሮቱን በፍጥነት ለመፍታት ከመሥራት ይልቅ “ልዩነቶችን ወደሚያሳድጉ እና ድህነትንና አለመመጣጠንን ወደሚያባብሱ ጦርነቶች” እየገባ መሆኑን በቁጭት ተናግረዋል።
የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በበኩላቸው በዓለም ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያላት ሀገራቸውን ከቅሬተ አካል ነዳጅ ለማራቅ እና የታዳሽ ሃይል ልማትን ለማፋጠን ጠንካራ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “መላው ዓለም እየተመለከተን ነው” ፣ “እናት ምድርም የወደፊት እጣ ፈንታዋን በመጠበቅ ወደ እኛ እየተመለከተች ነው ለዚህም ስኬታማ መሆን አለብን ሲሉ መናገራቸውን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።
የታንዛኒያዋ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሃሰን በበኩላቸው ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ጠይቀዋል።
ፕሬዚዳንቷ በተለይም አዳጊ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቁ መሆኑ ጠቅሰው፥ ሀገራትም የገቡትን ቃል እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!