Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“ቶዮታ ላንድ ክሩዘር 70” ከ40 ዓመታት በኋላ ለዓለም ገበያ ሊቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በየትኛውም መልክዓ ምድር ግልጋሎት እንዲሠጥ ታስቦ የተሠራው የጃፓኑ “ቶዮታ ላንድ ክሩዘር 70” ከ40 ዓመታት በኋላ በይበልጥ ዘምኖ ለዓለም ገበያ ሊቀርብ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ዘመናዊ መሣሪያዎች የተገጠሙለት “ቶዮታ ላንድ ክሩዘር 70” አሁን ላይ በጃፓን ለገበያ የቀረበ ሲሆን÷ በ2024 ደግሞ ለዓለም ገበያ ይቀርባል መባሉን ካርማግ የተሠኘ ስለ ተሽከርካሪዎች የሚዘግብ ገጽ አስነብቧል፡፡

በፈረንጆቹ 1984 ለመጀመሪያ ጊዜ ለገበያ የቀረበው “ቶዮታ ላንድ ክሩዘር 70”÷ ከ2004 ጀምሮ ከገበያ መጥፋቱ ተገልጿል፡፡

በተለምዶ “ሽሮ መልክ” በሚባል ቀለም እና ማራኪ ውጫዊ ገጽታ ለመጀመሪያ ጊዜ ለገበያ የቀረበው “ኤስ.ዩ.ቪ” (ስፖርት ዩቲሊቲ ቬይክል) ተሽከርካሪ በዘመናዊ መልኩ ለገበያ ሲቀርብ ውጫዊ ጥንካሬውን በማስጠበቅ ነው ተብሏል፡፡

ተሽከርካሪው ከ2 ነጥብ 8 ሊትር ቱርቦ የናፍታ ሞተር÷ 150 ኪሎ ዋት ኃይል እና 500 ኒውተን ሜትር ጉልበት እንደሚያገኝም ነው የተገለጸው፡፡

ሞተሩ ለአራቱም ጎማዎች እኩል ኃይል እንዲያደርስ ሆኖ (በ4 ዊል ድራይቭ) መሠራቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡

ፍጥነቱን እና ጥንካሬውን በሚመጥን መልኩ ማርሹን እስከ ሥድስት ድረስ መቀያየር እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡

የተሻሻለው “ቶዮታ ላንድ ክሩዘር 70” አሽከርካሪውን የሚያግዝ “ኤሌክትሪካል” የጥንቃቄ የፊት ጎማ መቆጣጠሪያ እንዲሁም የዳገት እና የቁልቁለት አጋዥ እና መቆጣጠሪያ ሥርዓት እንደተካተቱለትም ተጠቁሟል፡፡

“ዳሽ ቦርዱ” ቀለል ያለ፣ የተገጠመው “ተች ስክሪን” ከኋላ ያለውን ተሽከርካሪ መመልከት እና ማስጠንቀቅ የሚያስችል ሲያስፈልግም ስክሪኑ ላይ በመቀየር ሥልክ መደወል እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ግልጋሎቶችን መከወን የሚያስችሉ ዝመናዎች የተካተቱለት መሆኑን ነው ዘገባው ያመላከተው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version