ዓለምአቀፋዊ ዜና

ጊዜያዊ የተኩሥ አቁም ሥምምነቱ ማብቃቱን ተከትሎ እስራዔል ጋዛን መደብደብ ቀጥላለች ተባለ

By Alemayehu Geremew

December 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ሥምምነቱ ማብቃቱን ተከትሎ እስራዔል ጋዛን መደብደብ መቀጠሏ ተገለጸ፡፡

ኳታር ፣ ግብፅ እና አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ አሸማጋዮች የተኩስ አቁም ሥምምነቱ እስከ ዛሬ እንዲራዘም ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ÷ እስራዔል ጋዛ ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ለመቀጠል ዕቅድ እንዳላት አመላክተዋል፡፡

ከሰባተኛው ቀን የሰብዓዊነት ተኩሥ አቁም ሥምምነት በኋላ ዛሬ በቦንብና በመድፍ ታግዞ እንደገና የቀጠለው ጥቃት በንፁሐን ፍልሥጤማውያን ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ብሊንከን ማሳሰባቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ በጋዛ ከ15 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ሕይወታቸውን ሲያጡ በእስራዔል ደግሞ የሟቾች ቁጥር 1 ሺህ 200 ያህል መድረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡