የሀገር ውስጥ ዜና

ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ ጎበኙ

By Amele Demsew

November 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ፕሬዚዳንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) አስጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥” ወንድሜ ሼህ ሞሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንን ኢትዮጵያ ሀገራችን ለአየር ጠባይ ለውጥ መከላከል እየከወነች ያለችውን ተጨባጭ መፍትኄ ለማሳየት የቀረበችበትን የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) ስለጎበኙ አመሰግናለሁ”ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስራዋን በኮፕ28 ጉባኤ ላይ ባለው የኢትዮጵያ አውደ ርእይ (ፓቪሊዮን) በማስተዋወቅ ላይ እንደምትገኝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናሕያን ከዐውደ ርዕዩ ይፋዊ መክፈቻ አስቀድሞ ነው የኢትዮጵያን ፓቪሊዮን የጎበኙት።

#Ethiopia #UAE #COP28

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!