Fana: At a Speed of Life!

ኮፕ28 በዱባይ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ትኩረቱን ያደረገው ኮፕ28 ጉባኤ በዱባይ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል፡፡

በጉባዔው በተለይም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለም ክፍል ታይቶ አይታወቅም የተባለውን ከፍተኛ ሙቀት፣ የጎርፍ አደጋና የአየር ንብረት እያስከተላቸው ያሉ የተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከልና ጉዳታቸውን ለመቀነስ የሚረዱ ውሳኔዎች ይጠበቃሉ።

በዚህም በነዳጅ የበለጸጉ ሀገራት ላይ ግፊት ሲደረግ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡

በጉባዔው የዓለም መሪዎች፣ አክቲቪስቶች እና ከ97 ሺህ የሚልቁ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) እና አስተናጋጇ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጉባዔው ከፈረንጆቹ 2015 ከተካሄደው የፓሪሱ ጉባኤ ወዲህ እጅግ አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡

ሀገራት ከቅድመ-ኢንዱስትሪያል ዘመን ጀምሮ የአለም ሙቀት መጨመርን ከ2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በታች ወይም 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ለማድረግ መስማማታቸውን ፍራንስ 24 በዘገባው አንስቷል፡፡

ሆኖም የሳይንስ ሊቃውንት ዓለም እነዚህን ግቦች ለማሳካት ትክክለኛው መንገድ ላይ አይደለችም እያሉ ይገኛሉ፡፡

ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚደርሰውን አስከፊ ጉዳት ለመከላከል ፈጣን የሆነ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ይመክራሉ፡፡

በዚህ ጉባኤም አስፈላጊ ውሳኔዎችን በመውሰድ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመግታተት እንዲቻል ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

ለሁለት ሳምንት በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተላቸውን ቀውሶች ለመቀልበስ የሚያስችል ጠንካራ ውሳኔና እርምጃ ይተላለፍበታል ተብሎም ይጠበቃል።

#COP28UAE

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.