አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች 23 ነጥብ 1 ቢለየን ብር በላይ መከፈሉን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ባለሥልጣኑ በ2016 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት÷ለነዳጅ ኮንትሮባንድ ሽያጭ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን 65 በመቶ መቀነስ መቻሉን አስረድቷል፡፡
ከተቀመጠው አሠራር ውጭ አገልግሎት በማይሰጡና ነዳጅ ሣይቀዱ የድጎማ ክፍያ ለሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች ትብብር በሚፈፅሙ 5 ነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱንም ጠቁሟል፡፡
እስከ ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ ድረስም 23 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ለድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች መከፈሉን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚሁ መንገድ 120 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው የነዳጅ ግብይት የተፈጸመ ሲሆን÷የነዳጅ ስርጭት ቁጥጥርን ለማዘመን ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ጂ ፒ ኤስ እንዲገጥሙ መደረጉ ተገልጿል፡፡
ማደያ በሌለባቸው 556 ወረዳዎች አዳዲስ ማደያዎች እንዲገነቡ በተቀመጠው ዕቅድ መሰረትም በ8 ወረዳዎች አዳዲስ ማደያዎች ተገንበተው የነዳጅ ትስስር ፈቃድ ማግኘታቸው ተጠቅሷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!