የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎትን በሶማሌ ክልል አስጀመረ

By Amele Demsew

November 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎቱን በጅግጅጋ ከተማ አስጀምረዋል።

በመርሐ- ግብሩ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ የጂግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ በከተማዋ የተጀመረው የ 5ጂ አገልግሎት በርካታ አዳዲስ ስራዎችን ለመፍጠር እና ወደ ትግበራ ያልተለወጡ ሀሳቦች ለመቀየር ያግዛል፡፡

አገልግሎቱ የዲጂታል ኢኮኖሚውን በማሳለጥ የዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የምናደርገውን ጉዞ ያሳልጣልም ነው ያሉት፡፡

ጂግጅጋ ከተማ ከአዲስ አበባ እና አዳማ ቀጥሎ የ5ጂ አገልግሎት ይፋ የሆነባት ከተማ መሆኗንም ገልጸዋል፡፡

በቅድስት አባተ