የሀገር ውስጥ ዜና

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንብ እና የመመሪያዎች አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል ለፖሊስ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው

By Tibebu Kebede

May 25, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንብ እና መመሪያዎች አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል ለፖሊስ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ክፍተቶችን በማሻሻል የጋራ ግንዛቤ እና ወጥነት ያለው የህግ አተገባበር ስራ እንዲኖር ለፌደራል፣ለክልል እና ለከተማ ፖሊስ አመራሮች ስልጠናው እየተሰጠ ነው ብለዋል።