የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሃብቶች ያስተዋወቀ ፎረም በቤጂንግ ተካሄደ

By Alemayehu Geremew

November 28, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 18 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የቱሪዝም ፀጋዎችና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለቻይና ዜጎች ለማስተዋወቅ ያለመ የቱሪዝም ፕሮሞሽን ፎረም በቻይና ቤጂንግ ተካሂዷል፡፡

በፎረሙ ላይ በቻይና የሚገኙ አስጎብኚ ድርጅቶች እና በቱሪዝም ፕሮሞሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሃብቶች፣ ምርቶች እና የኢንቨስትመንት እድሎችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ ልማት የሰጠውን ልዩ ትኩረት በተመለከተም አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ ለቻይናውያን ጎብኚዎች ተመራጭ የሆኑ የቱሪዝም ምርቶችና አገልግሎቶች እየተስፋፉ መሆኑን ጠቅሰው፥ የኢትዮጵያን ፈርጀ – ብዙ የቱሪዝም መስህቦች እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በወቅቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል የቱሪዝም ትስስሮችንና ትብብሮችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።