አዲስ አበባ፣ ኅዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 32 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 3 ሺህ 100 ባለሐብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸው ተገለጸ፡፡
የክልሉ የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሕመድ እንድሪስ በክልሉ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው ብለዋል።
ለባለሐብቶቹ የመሬት አቅርቦትን ጨምሮ የብድርና የፋይናንስ አገልግሎት እንዲሁም ልዩ ልዩ የድጋፍ ማዕቀፎች እንደተዘረጉላቸውም ገልጸዋል፡፡
የኃይል አቅርቦት ችግር ቢያጋጥማቸውም ለመፍታት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ መደረሱን አቶ አሕመድ እንድሪስ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ባለሐብቶቹ በግብርና ፣በማምረቻው እና በአገልግሎት ዘርፍ መሰማራታቸውም ተገልጿል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከ7 ሺህ በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ለመቀበልና ወደ ሥራ ለማስገባት ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!