አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 18 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በቂ ዝግጅት እንደተደረገ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል፡፡
አቶ አገኘሁ ተሻገር በጅግጅጋ ከተማ በመገኘት ለበዓሉ እየተከናወነ ያለውን ዝግጅት ምልከታ አድርገዋል፡፡
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ሁስማን፥ ለ18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንደተሠሩ ጠቁመዋል።
ቀሪ ሥራዎች ቢኖሩም በቀጣዩቹ ቀናት በርብርብ እንደሚጠናቀቁ ያላቸውን እምነት ገልጸው፥ ክልሉን የማስተዋወቅ ሥራም በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በጅግጅጋ ከተማ ከሕዳር 25 እስከ ሕዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም በሚከናወኑ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ማጠቃለያውን ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዓሉ በሶማሌ ክልል አስተናጋጅነት “ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!