Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራ ክልል ከበጋ መስኖ ልማት 40 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከበጋ መስኖ ልማት 40 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገልጿል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ቃል ኪዳን ሽፈራው፥ በ2015/16 የመኸር እርሻ ሥራ ከለማው 5 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታር መሬት እስካሁን 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ ሰብል ተሰብስቧል ብለዋል።

ሰሊጥ፣ ማሾ፣ አኩሪ አተር እና የቢራ ገብስ በዘመናዊ እና ባሕላዊ መንገድ በመታገዝ የመሰብሰብ ሥራው በመጠናቀቅ ላይ መኾኑንም ተናግረዋል።

በክልሉ ሰፊ የምርት ሽፋን ያላቸውን የስንዴ፣ የጤፍና የበቆሎ ሰብሎችን የመሰብሰብ ሥራም ተጀምሯል ነው ያሉት።

በዘመናዊ መንገድ ለመሰብሰብ በክልሉ ከሚገኙ ባለሐብቶች እና ማኅበራት ኮምባይነር የማስገባት እንቅስቃሴ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version