ኢትዮጵያ የትሬድማርክ አፍሪካ ብሄራዊ ቁጥጥር ኮሚቴ አመራር አካላት የጋራ አህጉራዊ መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በታንዛኒያ ዳሬሰላም እየተካሄደ በሚገኘው የትሬድማርክ አፍሪካ ብሄራዊ ቁጥጥር ኮሚቴ አመራር አካላት የጋራ አህጉራዊ መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ካሳሁን ጎፌ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷የትሬድማርክ አፍሪካ ብሄራዊ ቁጥጥር ኮሚቴ አመራር አካላት የጋራ መድረክ በታንዛኒያ ዳሬሰላም እየተካሄደ በሚገኘው አህጉራዊ መድረክ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን አስታውቀዋል።
በመድረኩ በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚደረገውን የንግድ ትስስር እና ልውውጥ በማሳለጥ ረገድ የተከናወኑ ስራዎች በጥልቀት ይገመገማሉ ተብሏል፡፡
የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠናና ሌሎች የነፃ ንግድ ቀጠናዎች ትግበራ ላይ ያሉ መልካም ልምዶች ቀርበው ወይይት የሚደረግባቸው ይሆናል ነው የተባለው።
በመቀጠልም ብሄራዊ ቁጥጥር ኮሚቴ ትኩረት ቢያገኙ በሚላቸው ጉዳዮችና እንደ ተሞክሮ ሊወሰዱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚደረግም ጠቅሰዋል፡፡