አዲስ አበባ፣ ኅዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ያለ አገልግሎት የቆሙ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ በማስወገድ ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ።
ተሽከርካሪዎቹ በክልሉ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ለበርካታ ጊዜ የቆሙ ነበሩ ተብሏል፡፡
የክልሉ የግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የሚወገዱ ንብረቶች ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ሳምሶም ዋቅወያ በጉዳዩ ማብራሪያ ለመሥጠት ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ነበራቸው፡፡
በቆይታቸውም በያዝነው በጀት ዓመት 3 ወራት ብቻ በክልሉ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የቆሙ 54 ተሽከርካሪዎችን በጨረታ በሽያጭ እንዲወገዱ መደረጉን ተናግረዋል።
ከሽያጩም 25 ሚሊየን 217 ሺህ 822 ብር ለክልሉ መንግሥት ገቢ መደረጉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ተቋሙ የተለያዩ ብረቶችን በጨረታ በሽያጭ እንዲወገዱ የማድረግ ሥራ መሥራቱን አስረድተዋል።
በታሪክ አዱኛ