Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በፆታዊ ጥቃት ላይ በሚመክረው መድረክ ለመካፈል ደቡብ አፍሪካ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃት ለማስቆም በሚመክረው ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ገብተዋል፡፡

ጉባዔው ትናንት የተጀመረ ሲሆን እስከዛሬ እንደሚቀጥል በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል፡፡

በቦታው በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር አብዱ (ዶ/ር) ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በጉባዔው የሀገራት መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የግሉ ዘርፍ፣ ሲቪል ማኅበራት፣ ምሁራን ወጣቶችና ሴቶች በአፍሪካ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመቅረፍ ተግባር ተኮር ሥልቶች ላይ እንደሚወያዩም የአፍሪካ ኅብረት መረጃ ያመለክታል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version