Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

32ኛው ሀገር ዓቀፍ የትምህርት ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 32ኛው ሀገር ዓቀፍ የትምህርት ጉባዔ “የትምህርት ጥራት ለሁለንተናዊ ዕድገት “በሚል መሪ ሃሳብ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው ላይ የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና፣ የክልል የትምህርት ዘርፍ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ተገኝተዋል።

ጉባኤው በዛሬው ውሎው:- የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ አቅጣጫዎች፣ የመውጫ ፈተና አፈፃፀምና ቀጣይ አቅጣጫዎች፣ የመምህራን ልማት እና አስተዳደርን ጉዳዮች እና የመረጃ ስርዓት ተግዳሮትና ተዓማኒነት ጥናታዊ ሪፖርት የሚቀርብ መሆኑን ከወጣው መርሃግብር ለመረዳት ተችሏል።

ጉባዔው ነገ ሕዳር 19 በተለያዩ ጉዳዮች መክሮ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ጉባዔውን የትምህርት ሚኒስቴር፣ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እና የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ በጋራ ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ÷ በትምህርት ሥርዓቱ እየተደረገ ያለው ማሻሻያ ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን በበኩላቸው ÷ በክልሉ የተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን በመቋቋም የትምህርት ተቋማትን በማስፋፋትና ጥራትን በማረጋገጥ አበረታች ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግሥት በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያለውን ስብራት ለመጠገን ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝም በጉባኤው ተነስቷል።

በመራኦል ከድር

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version