የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኦስትሪያ መራሄ መንግሥት ካርል ኔሃመር ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

November 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው በኦስትሪያው መራሄ መንግሥት ካርል ኔሃመር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ከአቀባበሉ በኋላም ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በኢትዮ- ኦስትሪያ ግንኙነት፣ በልማት ትብብር እና በሌሎች ጠንካራ ትብብር ሊመሰረትባቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡