የሀገር ውስጥ ዜና

ንግድ ባንክ በ”ቢክ ኢትዮጵያ” የፋይናንስ አገልግሎት ውድድር አሸናፊ ሆነ

By Amele Demsew

November 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ”ቢክ ኢትዮጵያ” የተዘጋጀውን የፋይናነስ አገልግሎት አሰጣጥ ውድድር አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳዲስ የስራ ዕድሎችን ለሚፈጥሩ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በሚያቀርበው የብድር አገልግሎት ውድድሩን ሊያሸንፍ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ÷ የባንክ ተጠቃሚ ላልነበሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን በማዳረስ እና ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ በተንቀሳቃሽ ንብረት ዋስትና የገንዘብ ብድር አገልግሎት በመስጠት ውድድሩን ማሸነፍ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

ለዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእውቅና የምስክር ወረቀት እና የገንዘብ ሽልማት እንደተበረከተለት ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ቢክ ኢትዮጵያ የቢክ አፍሪካ ቅርንጫፍ ሲሆን ፥ በስራ ፈጠራ ለተሰማሩ እና የስራ እድል ለሚፈጥሩ ተቋማት ክህሎትን በማጋራት አፍሪካ ከአውሮፓ ጋር የተቀላጠፈ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትስስር እንዲኖር የሚረዳ ተቋም ነው።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/

ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!