Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የባሕር ኃይሉ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል ተሰማራ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል በምሥራቅ ኢትዮጵያ እየዘነበ ያለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ጉዳት እንዳያደርስ ቀድሞ ለመከላከል ወደ አካባቢው ተሰማርቷል፡፡

የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለ ማርያም (ዶ/ር) ለባሕር ኃይሉ አቀባበል ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት÷ የባሕር ኃይል አባላቱ ሥራ የተቃና እንዲሆን አሥፈላጊው ትብብር ይደረጋል፡፡

በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን በሚገኙ ሥምንት ወረዳዎች በተከሰተው የጎርፍ አደጋም የባሕር ኃይሉ ሞያዊ ብቃቱን ተጠቅሞ ሥራውን እንደሚሠራ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የባሕር ኃይል ትምህርትና ሥልጠና ኃላፊ እና የቡድኑ አስተባባሪ ኮሎኔል ከበደ ሚካኤል በበኩላቸው ÷ የተሰጠንን ሀገራዊ ግዳጅ ተረክበን ለመፈፀም ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version