አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ያለው ትምህርት በማቅረብ የሚመራመርና በሥነ-ምግባር የታነጸ ዜጋ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ፡፡
ከ32ኛው የትምህርት ጉባኤ ትይዩ የቅድመ ጉባኤ መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሽኔ ÷በቀጣይ ሁለት ዓመታት 8 ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ያለው ትምህርት በማቅረብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም፣የሚመራመርና በሥነ-ምግባር የታነጸ ዜጋ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
የጉባዔው ዓላማ በከፍተኛ ትምህርቱ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ በመወያየት በቀጣይ ስለሚወሰዱ የእርምትና የለውጥ እርምጃዎች የጋራ ግንዛቤና አቋም ለመያዝ መሆኑን ጠቁመዋል።
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በሽር አብዱላሂ (ዶ/ር)ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት÷ ዩኒቨርሲቲው በተፈጥሮ ሀብት፣ እርብቶ አደርና እንስሳት ልማት ፣ በምግብ ዋስትና ፣ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ መስክ እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
በመራኦል ከድር
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!