Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከ220 ሚሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትለቲክስ ፌዴሬሽን 27ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2016 ዓመት ከ220 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

በጀቱ ለስልጠና እንዲሁም ለስፖርታዊ ውድድሮች ማካሄጃ ጭምር የሚውል መሆኑ ነው የተገለጸው።

የወጣቶች የፕሮጀክት ስልጠና በበጀቱ ሊካተት እንደሚገባም የጉባኤው ተሳታፊዎች ተስማምተዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በዚሁ ጊዜ እንደገለጸችው ÷ ሀገራችንን በዓለም አደባባይ ይበልጥ ከፍ ለማድረግና የዘርፉን የገቢ ምንጭነት ለማሳደግ ከክልል ፌዴሬሽኖች ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በበኩላቸው ÷ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠብቀውን ውጤት የሚያመጡ አትሌቶችን በብዛት ለማፍራት ክልሎች ከፌዴራል ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ስፖርት ለሀገር ሰላምና ፍቅር እንዲሁም አንድነትና ልማት መረጋገጥ ዓይነተኛ መሳሪያ በመሆኑ አሰልጣኞችና አመራሮች ለተግባራዊነቱ ግንባር ቀደም ሊሆኑ እንደሚገባም ነው የገለጹት።

ለበጀት አጠቃቀምና ለስፖርት ስነ ምግባር ትኩረት መሰጠቱንም አምባሳደር መስፍን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በጉባኤው የተሳተፉት የክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች እንዳሉት ፥ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የሚያግዝ የወዳጅነት ውድድር ለማካሔድና ተተኪ ወጣቶችን ለማፍራት በትኩረት ይሰራሉ፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version