አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ዘለቄታ ያለው አማራጭ የአውሮፕላን ነዳጅ ለማምረት የሚያስችላትን ድጋፍ አገኘች፡፡
ድጋፉ የተገኘው በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ከመደበኛዉ ነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ተኮር ነዳጅ በዘላቂነት ለመሸጋገርና የአቪዬሽን በካይ ጋዞችን ልቀት እስከ ፈረንጆቹ 2050 የተጣራ ዜሮ ለማድረስ በተያዘው ዕቅድ መሠረት ነው፡፡
ለዚህም ደረቅ የተፈጥሮ ምርቶች ዕፅዋት እና ሌሎች መሠል አነስተኛ የብክለት ደረጃ ያላቸው ግብዓቶች ጥቅም ላይ ይውላሉ ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ከፈረንጆቹ ኅዳር 20 እስከ 24 በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዱባይ እየተካሄደ ባለው 3ኛዉ የአቪዬሺንና አማራጭ ነዳጅ ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች፡፡
ዘላቂነት ያለዉ የአቪዬሽን ነዳጅ ልማትን የተመለከቱ ጥናቶችን ለማድረግ የሚረዳ የፋይናንስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ የተደረገው ከኮንፈረንሱ ጎን ለጎን ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በተካሄደው የሁለትዮሽ ውይይት መሰረት መሆኑን ከትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ድጋፉ ይፋ በሆነበት መርሐ-ግብር ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደንጌ ቦሩ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ ተገኝተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!