የሀገር ውስጥ ዜና

ዛሬ በመላው ሃገሪቱ 1 ሺህ 441ኛው ኢድ አልፈጥር በአል ተከበረ

By Meseret Awoke

May 24, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በመላው ሃገሪቱ 1 ሺህ 441ኛው የኢድ አልፈጥር በአል ተከበረ።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ የረመዳንን ጾም መገባደድ ተከትሎ የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በአል በመላው የሃገሪቱ በተለያየ መልኩ ተከብሮ ውሏል።