Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

20 ነጥብ 7 ሚሊየን የመማሪያ መጽሐፍ ሕትመት ታዘዘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደ ሀገር የተፈጠረውን የመማሪያ መጽሐፍ እጥረት ለመፍታት የ20 ነጥብ 7 ሚሊየን መጽሐፍ ሕትመት መታዘዙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)÷የሕትመት ሥራው እስካሁን የዘገየው ከአዲሱ የትምርት ሥርዓት ትግበራ ጋር በተያያዘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እስካሁን 10 ሚሊየን 640 ሺህ መጽሐፍ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ስርጭት መድረጉንም አስረድተዋል፡፡

የፊታችን ታሕሳስ ወር መጨረሻ ድረስ ሀገር ውስጥ በማስገባት በ3 ሳምንት ውስጥ ሙሉ ስርጭት እንደሚደረግ ሚኒስትሩ አመላክተዋል፡፡

እስከ ትምህርት ዓመቱ አጋማሽ 1 መጽሐፍ ለ4 ተማሪዎች የሚደረስ ሲሆን÷በቀጣይ ዓመትም የመጽሐፍ እጥረቱን በመቅረፍ 1 ለ 2 ለማዳረስ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ለመጽሐፍ ሕትመቱም መንግስት 40 ሚሊየን ዶላር ወጪ ማድረጉን ነው  የተናገሩት፡፡

በአሸብር ካሳሁን

Exit mobile version