አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋና አዲስ ለአንድ ወር የሚቆይና ለጎብኚዎች የሚያገለግል የመዳረሻ የቱሪስት ቪዛ ይፋ ማድረጓን የሀገሪቱ ቱሪዝም ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
በዚህም መሰረት ጎብኝዎች በፈረንጆቹ ከታህሳስ 1 እስከ ጥር 14 ድረስ ከመደበኛው የቪዛ ፈቃድ ውጭ ወደ ጋና በመጓዝ ጉብኝት ማድረግ ይችላሉ ተብሏል፡፡
በተለይም የቪዛ ሂደቱ ቀላል እንዲሆን መደረጉ ቱሪስቶች ሳይቸገሩ ወደ ጋና በመግባት ታሪካዊ ስፍራዎችን፣ ቅርሶችን እና ፌስቲቫሎችን እንዲታደሙ ያስቻላቸዋል ብሏል፡፡
አዲሱ የቪዛ ሂደት በጋና “ቢዮንድ ዘ ሪተርን” የተባለው የ10 ዓመት የቱሪዝም ኢኒሺየቲቭ አካል መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ኢኒሺየቲቩ ጋናን የቱሪስት እና የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
‘ታህሳስን በጋና’ የተባለው የጎዳና ላይ ፌስቲቫል ከታህሳስ 14 ጀምሮ በአክራ መከበር ይጀምራል የተባለ ሲሆን ዳያስፖራዎች እና የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች ይሳተፋሉ መባሉን ግራፊክ ኦንላይን አስነብቧል፡፡