አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከዩክሬን የሰላም ድርድር ዙሪያ ተስፋ አጥቆርጥም ሲሉ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ፡፡
ፕሬዚዳንቱ በቡድን 20 አባል ሀገራት ሰብሰባ ላይ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እስካሁን የተደረጉ የሰላም ስምምት ሙከራዎችን ውድቅ አለማድርጓን አስታውሰዋል፡፡
በአንፃሩ ኬቭ ከሞስኮው ጋር ድርድር ለማድረግ በሯን ዝግ ማድረጓን ነው ያስረዱት፡፡
እንደማንኛውም ወታደራዊ ግጭት ጦርነቱ ለሁለቱ ሀገራት አሳዛኝ ክስተትን ፈጥሯል ያሉት ፑቲን÷ ጦርነቱን እንዴት ማቆም እንደሚቻል ማስብ ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ ከዩክሬን የቀረበላትን የሰላም ስምምነት ውድቅ አላደረገችም፣ ነገር ግን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር የሰላም ስምምነት እንዳይደረግ ህጋዊ ፊርማቸውን አስቀምጠዋል ብለዋል፡፡
ባለፈው ዓመት የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ፑቲን የሩሲያ ፕሬዚዳንት ሆነው እስከቆዩ ድረስ ከክሬምሊን ጋር ማንኛውንም የሰላም ድርድር ላለማደረግ የሚደነግገውን ህግ ፈርመው ማፅደቃቸውን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።