Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ክልሉን የትርምስ ቀጣና ማድረግ ለአማራ ሕዝብ አይበጅም – የደቡብ ወሎ ዞን

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች እናስመልሳለን በሚል ሽፋን ክልሉን የትርምስ ቀጣና ማድረግ ለአማራ ሕዝብ እንደማይበጅ የደቡብ ወሎ ዞን አስገነዘበ፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ከተማ በወቅታዊ የሠላምና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ የሚያገኙት ሕግና ሥርዓትን በተከተለ መንገድ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዓሊ መኮንን በውይይቱ ላይ አስገንዝበዋል፡፡

የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች እናስመልሳለን በሚል ሽፋንም ኅብረተሰቡን ለእንግልትና ስቃይ መዳረግ እንደማይባ መግለጻቸውንም አሚኮ ዘግቧል፡፡

የደቡብ ወሎና የደሴ ከተማ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴየር ጀኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ÷ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች የሚመለሱት ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከርና በሰላማዊ መንገድ በመታገል እንጅ እርስ በእርስ በመገዳደል አይደለም ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሠላም እንዲሰፍን መንግሥት በቁርጠኝነት ከሕዝቡ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሐይማኖት አባቶች ጋር በቅንጅት እንዲሠራ ጠይቀዋል፡፡

በወረዳው በፀጥታ ችግር ምክንያት 22 ትምህርት ቤቶች ሥራ አለጀመራቸው እና የንፁህ መጠጥ ውኃ መቋረጡምን አንስተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version