የሀገር ውስጥ ዜና

የተመድ ኤጀንሲዎች ለኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ተግባራዊነት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለጹ

By Alemayehu Geremew

November 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ላይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጄንሲዎች ጋር መክሯል፡፡

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጄንሲዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

መንግስት መረጃና ስታትስቲክስ ለሀገር ልማትና እድገት የሚያበረክተውን ከፍተኛ ጥቅም በመረዳት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ነመራ ገበዬሁ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የየኤጄንሲዎቹ ተወካዮችም መንግስት ለስታትስቲክስ ልማት የሰጠውን ትኩረት አድንቀው÷ ለተግባራዊነቱም ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡