የሀገር ውስጥ ዜና

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሕዝቡ ጋር መከረ

By Alemayehu Geremew

November 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከሕዝቡ ጋር መክሯል፡፡

መድረኩ ከብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የአደረጃጀት ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ ዓለሙ ሰውነት÷ በወቅታዊ የፀጥታና የልማት ሥራዎች እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ለውይይት የሚሆን መነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡

የ76ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ በበኩላቸው የሰላም ባለቤት ሕዝቡ በመሆኑ ከጸጥታ አካላት ጎን ሆኖ ሠላሙን እንዲያረጋግጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎችም የአካባቢያቸውን ዘላቂ ሠላም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን ለማስጠበቅ እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡