Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቤጂንግ የውጭ ጉዳይ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ በአማርኛ ቋንቋ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤጂንግ የውጭ ጉዳይ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮ-ቻይና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ መጎልበት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ትምህርት ጥናት ላይ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዳይሬክቶሬት አባላት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሰን ዮዥንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅትም ሰን ዮዥንግ እንደገለጹት÷ ዩኒቨርሲቲው በአማርኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በያዝነው ዓመት ያስመርቃል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው÷ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ ሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን እንዲያስተምር ጠይቀዋል፡፡

ዘንድሮ በአማርኛ ቋንቋ የሚመረቁትም የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት አምባሳደሮች ናቸው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version