አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ከዕዳ ወደ ምንዳ’ በሚል መሪ-ሐሳብ በተለያዩ ማዕከላት ሲሰጥ የቆየው 3ኛ ዙር የመንግሥት አመራሮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ።
3ኛው ዙር የአቅም ግንባታ ሥልጠና ከመላ ሀገሪቱ ለተወጣጡ የመንግሥት አመራሮች ላለፉት 12 ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ሥልጠናው የተለያዩ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታን መነሻ ያደረጉ ጽንሰ-ሐሳቦች ላይ ትኩረት አድርጎ መሠጠቱን ከብልጽግና ፓርቲ ጽኅፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከማዕከል ሥልጠና በሻገር ሰልጣኞቹ በሕዝብና መንግስት እንዲሁም በግሉ ዘርፍ እየተሠሩ ያሉ ተቋማትንና መሠረተ ልማቶች መጎብኘታቸውም ነው የተጠቀሰው፡፡
በሥልጠናዉ ጊዜውን የሚዋጅ አመራር ለመፍጠር እንደሚያስችል የተገለጸ ሲሆን፤ ሠልጣኝ አመራሮቹም ከመላ ሀገሪቱ ተዉጣጥተዉ መሰልጠናቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ተነግሯል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!