ጊኒ የቀድሞ ፕሬዚዳንቷን በሀገር ክህደት ወንጀል ምርመራ ላካሂድባቸው ነው አለች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጊኒ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ በሀገር ክህደት ወንጀል ምርመራ ሊካሄድባቸው እንደሆነ ተገለጸ።
የጊኒ የፍትህ ሚኒስትር አልፎንሴ ቻርለስ ራይት፥ የቀድሞው የሀገራቸው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ከተወገዱ ከሁለት ዓመት በኋላ በሀገር ክህደት ወንጀል ምርመራ እንደሚካሄድባቸው አስታውቀዋል።
በጊኒ የመጀመሪያው በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ መሪ በሚል የሚታወቁት ኮንዴ በኮሎኔል ማማዲ ዱምቡያ በሚመራው ጦር በሃይል ከስልጣን መነሳታቸው ይታወቃል።
መፈንቅለ መንግስቱ የመጣው ለሦስተኛ የስልጣን ዘመን ራሳቸውን ለምርጫ ባጩበት ወቅት ሲሆን፥ ለ10 ዓመታት የዘለቀውን የስልጣን ጊዜ ለማራዘም ያለመ እንደነበር ተጠቅሷል።
በዚህ ሂደትም የሚነሱ ተቃውሞዎችን የሃይል እርምጃ መውሰዳቸውም ነው የተነሳው።
የጊኒ ወታደራዊ መሪዎች ሙስና፣ ግድያና አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ በኮንዴ ላይ በርካታ ምርመራዎችን ተጀምረዋል።
በጊኒ ዋና ከተማ ኮናክሪ ለሚገኘው የህዝብ ዐቃቤ ሕግ በተላከው ደብዳቤ፥ የቀድሞው ፕሬዚዳንት በሀገር ክህደት፣ የወንጀል ሴራዎችን በማቀነባበርና ከህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡
አሁን ኮንዴ በስደት ቱርክ እየኖሩ ነው መባሉን የዘገበው አልጄዚራ ነው፡፡
#Guinea
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!