Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ የስለላ ተግባር የሚያከናውን ሳተላይት በተሳካ ሁኔታ ወደህዋ ማምጠቋን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ የስለላ ተግባር የሚያከናውን ሳተላይቷን በተሳካ ሁኔታ ወደ ህዋ ማምጠቋን ገልጻለች፡፡
 
በዚህ ዓመት ያደረገቻቸው ሁለት ሙከራዎች የከሸፉባት ሰሜን ኮሪያ የአሁኑን ሳተላይት በተሳካ ሁኔታ ማምጠቅ የቻለችው በሩሲያ እርዳታ መሆኑ ተነግሯል፡፡
 
በፈረንጆቹ መስከረም ወር ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንና ኪም ጆንግ ኡን የተገናኙ ሲሆን ሞስኮ ለፒዮንግያንግ በጠፈር መርሃ ግብሯ እርዳታ በምትሰጥበት ሁኔታ ላይ መክረዋል ተብሏል።
 
ሳተላይቱ ወደ ስራ መግባቱን እስካሁን አላረጋገጥኩም ያለችው ደቡብ ኮሪያ ነገር ግን ሰሜን ኮሪያ ከሩሲያ እርዳታ እንዳገኘች እምነት እንዳላት ገልፃለች፡፡
 
እርምጃውን ተከትሎ ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የምታደርገውን ቁጥጥር ዳግም እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡
 
ሁለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ 2018 ወታደራዊ ውጥረትን ለማርገብ ከተስማሙባቸው ጉዳዮች ከፊሉን ለማገድ እርምጃዎችን እንደምትወስድም ገልፃለች።
 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) እንዲሁም አሜሪካና ጃፓንን ጨምሮ ሌሎች ሀገራትም ድርጊቱን ማውገዛቸው ተመላክቷል፡፡
 
የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሰሜን ኮሪያ በባለስቲክ ሚሳኤል ቴክኖሎጂ ታግዛ የምታከናውነው የትኛውም ድርጊት ከፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች ጋር የሚቃረን ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
 
አያይዘውም ሰሜን ኮሪያ ኒውክሌርን ወደ ማስወገዱ መንገድ እንድትመለስ ጥሪ አቅርበዋል።
 
አሜሪካ በበኩሏ እርምጃውን በተመድ ውሳኔዎች ላይ የተፈጸመ አስከፊ ጥሰት ስትል ኮንናለች።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.