Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት ይገባል- አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘላቂ ሰላምና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ አሳሰቡ።

3ኛው ዙር “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርዕስ ሲካሄድ የቆየው የመንግሥት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የማጠቃለያ ስነ -ስርዓት ተከናውኗል።

በመርሐ- ግብሩ ላይ በእንግድነት የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ ብልጽግና መላው ኢትዮጵያዊያንን በአንድ ገመድ ያስተሳሰረ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ አያይዘውም÷ ያስተሳሰረን ገመድ እንዳይበጠስ ሁላችንም ሃላፊነት ወስደን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።

የአማራ ህዝብ ሰላም፣ልማት፣ ውስጣዊ አንድነትና አብሮነትን ይፈልጋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ዘላቂ ሰላምና የህግ የበላይነትን በማስፈን የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአማራ ክልል የህዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት አማካሪ እና የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ይርጋ ሲሳይ በበኩላቸው ÷አመራሩ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት በማጠናከር ለስኬትና ለውጤት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ሰልጣኞቹ ከወር ደመወዛቸው በመሰብሰብ በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል 447 ሺህ370 ብር ለክልሉ መንግስት ድጋፍ ማድረጋቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመልክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version