አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪቲሽ ቤተ – መጻሕፍት በፈረንጆች ጥቅምት 31 ባስተናገደው የሳይበር ጥቃት የሰራተኞቼ የግል መረጃ መውጣቱን አረጋግጫለሁ ብሏል።
የሳይበር ጥቃቱ የቤተ- መጻሕፍቱን ድረ-ገጽ ለአንድ ወር ያህል እንዲቋረጥ ማድረጉም ነው የተገለጸው።
የሳይበር ዘራፊዎች ፓስፖርትን ጨምሮ የመረጃ ዋጋቸውን 596 ሺህ 459 ዩሮ ተምነዋልም ተብሏል፡፡
የብሪቲሽ ቤተ መጻሕፍት በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት “ባለፈው ሳምንት በተከሰተ የሣይበር ጥቃት የሰራተኞች አንዳንድ የግል መረጃዎች ሾልከው መውጣታቸውን ገልጿል፡፡
ሆኖም ግን የተጠቃሚዎች መረጃ ለጥቃት ስለመዳረጉ ምንም ዓይነት ማስረጃ እንደሌለና እየተሸጠ ያለው መረጃ የብሪቲሽ ቤተ-መጻሕፍት ሰራተኞች መሆን አለመሆኑን አላረጋገጥኩም ብሏል፡፡
የሀገሪቱ የሳይበር ደህንነት ማዕከል ቃል አቀባይ እንደገለጸው ፥ ችግሩን ለመፍታት ከብሪቲሽ ቤተ-መጻሕፍት ጋር እየሰራ ነው ።
‘ራንሰምዌር’ የሚባለው የሳይበር ጥቃት ገንዘብ ካልተከፈለ መረጃ ሾልኮ የወጣበት አካል የግሉን መረጃ እስከመጨረሻው እንዳይገኝ የሚያደርግ ‘ክሪፕቶቪሮሎጂካል ‘የሚባለው የጥቃት ዓይነት ነው።
‘ራንሰምዌር’ የብሪታኒያ የሳይበር ስጋት ነው ያሉት ቃላቀባዩ፤ ሁሉም ድርጅቶች አውታረ መረቦቻቸውን ለመጠበቅ መፍትሄ ብለን ያስቀምጥናቸውን መከተል አለባቸው ሲሉም ነው ማስጠንቀቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከጥቃቱ ጀርባ ‘ሪሂሲዳ’ የተባለ የራንሰምዌር ቡድን እንዳለ እና የተለያዩ ሰነዶችን የሚያሳይ ምስል በገጹ ማጋራቱም ነው የተገለጸው።
ቢቢሲ በዘገባው መረጃው እውነት ይሁን ሀሰት ማረጋገጥ እንዳልቻለም ጠቁሟል፡፡
የሳይበር ወንጀለኞቹ “ልዩ እና አስደናቂ መረጃ” በሚል ጨረታ ያወጡ ሲሆን ጨረታውም ከፈረንጆቹ ሕዳር 27 በፊት እንደሚያበቃ ማስታወቂያ መሰል ዛቻዎችን መልቀቃቸውም ነው የተነገረው፡፡
በፈረንጆቹ ሕዳር 15 ኤፍቢአይ ፣የአሜሪካ የሳይበር ደህንነት እና የመሠረተ ልማት ደህንነት ኤጀንሲ በራሂሲዳ ስጋት አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው በመረጃው ተጠቅሷለ።
እነዚህ አካላት በጋራ ባወጡት መግለጫም ፥ ቡድኑ በትምህርት፣ በጤና አጠባበቅ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ላይ እንደሚያነጣጥሩ ተገልጿል።
ቡድኑ በቅርብ ጊዜ በቺሊ ጦር፣ በፖርቱጋል ከተማ ጎንዶማር እና በዌስት ስኮትላንድ ዩኒቨርሲቲ ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ጀርባ እጁ እንዳለበት ተመላክቷ