የሀገር ውስጥ ዜና

ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅመማ ቅመም ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

By Alemayehu Geremew

November 21, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 12ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅመማ ቅመም ጉባዔ “ኢትዮጵያ ለግብርና ምርት ፍላጎት አስተማማኝ ምንጭ” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ዓለም አቀፍ ጉባዔውን የኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ ቅባት እህሎችና ቅመማ ቅመም አዘጋጅቶ ላኪዎች ማኅበር፣ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።

በጉባዔው ከ400 በላይ የሀገር ውስጥ ላኪዎች፣ የእርሻ ግብአትና ማሽነሪ አቅራቢዎች፣ የጉምሩክ አስተላላፊዎች፣ እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ዓለምአቀፍ ምርት ገዥ ኩባንያዎች እየተሳተፋ ነው።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ገብረመስቀል ጫላ በጉባዔው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው የግብርና ምርቶች የጥራጥሬና ቅመማ ቅመም ዋነኞቹ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡