Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ብራዚል በታሪኳ ከፍተኛ የተባለለትን የሙቀት መጠን አስመዘገበች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚል በታሪኳ ከፍተኛ የተባበለለትን 44 ነጥብ 8 ዲግሪ ሴሊሺየስ የሙቀት መጠን አስመዝግባለች፡፡
 
ይህ ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበው በብራዚል ደቡብ ምስራቅ ሚናስ ገራይስ በምትገኘው አራኩዋይ ከተማ እንደሆነ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
 
ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቀው ሙቀት በኤልኒኖ እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተከሰተ መሆኑም ተመላክቷል።
 
ይሁንና የሙቀት መጠኑ በዚህ ሳምንት ሊቀንስ እንደሚችል የአየር ትንበያ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
 
የሀገሪቱ ብሔራዊ የሚቲዮሮሎጂ ተቋም ኃላፊዎች ሦስት የግዛት ዋና ከተሞች ብቻ ወደ 40 ዲግሪ ሴሊሺየስ የቀረበ የሙቀት መጠን እንደሚመዘገብባቸው ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
 
በአራኳይ የተመዘገበው 44 ነጥብ 8 ዲግሪ ሴሊሺየስ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 2005 ከተመዘገበው 44 ነጥብ 7 ዲግሪ ሴሊሺየስ ክብረወሰን የሰበረ መሆኑን ተቋሙ አመላክቷል።
 
ሙቀቱ በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወቅት ከመጀመሩ አንድ ወር በፊት መከሰቱ በመላ ሀገሪቱ የማንቂያ ደውል ሆኗል ተብሏል።
 
ሰዎች ሙቀቱን ለመከላከል የሚያደርጉት ጥረትም የብራዚል የኃይል ፍጆታ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version