አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን 100 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ተጨማሪ ወታደራዊ ዕርዳታ እንደምትሰጥ አስታወቀች፡፡
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ሀገራቸው ለዩክሬን የምታደርገው ድጋፍ ቃል በተገባው መሰረት እንደሚፈጸም ማረጋገጣቸውም ነው የተገለጸው፡፡
በዚህ የጦር መሣሪያ ድጋፍ ስቲንገር ፀረ አውሮፕላን ሚሳኤሎች መካተታቸው የተገለጸ ሲሆን፥ የተለያዩ ተተኳሾች፣ አነስተኛ እና ከፍተኛ የጦር መሳሪያዎች ከድጋፉ መካከል ይገኙበታል ብሏል የአሜሪካ መከላከያ ዲፓርትመንት፡፡
ከነሐሴ 2021 ጀምሮ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለዩክሬን 51ኛው ዙር ወታደራዊ እርዳታን ከመከላከያ ዲፓርትመንት የጦር መሳሪያዎች ክምችት መስጠቱም ነው የተነገረው፡፡
ሎይድ በዩክሬን ከሀገሪቱ አመራሮች ጋር ውይይት ለማድረግ መገኘታቸው የተጠቀሰ ሲሆን፥ በዚህ ጊዜም “አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገው ቀጣይነት ያለውን የደህንነት እርዳታ ነው” ሲሉ አስምረውበታል፡፡
እየተካሄደ ባለው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት የዩክሬን የወደፊት ኃይል ርዕይ ላይ ፔንታጎን መግለጫ ሰጥቷል ሲል የዘገበው ዢኑዋ ነው፡፡
#US #Ukrain #Russia #MilitaryAid
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!