Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ለንደን ጋትዊክ በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ለንደን -ጋትዊክ ከተማ በረራ ጀመረ።

በማስጀመርያ መርሐ ግብሩ ÷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ፣ የዓየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ኃላፊ ለማ ያዴቻ እና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልሽ ተገኝተዋል፡፡

በሳምንት ሦስት ጊዜ የሚደረገው በረራ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክር ተመላክቷል፡፡

ጋትዊክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእንግሊዝ ሦስተኛው መዳረሻ ነው ተብሏል፡፡

ዓየር መንገዱ ወደ ለንደን ጋትዊክ በረራ መጀመሩን ተከትሎም አጠቃላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹ 136 መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

በፍቅርተ ከበደ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version