የሀገር ውስጥ ዜና

በአይሻ (ኢ/ር) የተመራ ልዑክ በደቡብ ኮሪያ የሲየንግ አፕ ግድብን ገበኘ

By Feven Bishaw

November 20, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) የተመራ ልዑክ የጄጁ ራስ አስተዳደር ግዛት የኮሪያ ገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን ሪጂን ዋና መ/ቤትን ጎብኝቷል፡፡

የኮሪያ ገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን የሪጂን ዋና መ/ቤት ዳይሬክተር ጄኔራል ዶንግ ቺኦል እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ለልዑካን ቡድኑ አባላት አቀባበል እና ገለጻ አድርገዋል፡፡

በቀጣይል የልዑካን ቡድኑ አባላት የደቡብ ኮሪያ የሲየንግ አፕ ግድብ የተገነባበትን ቦታ በአካል በመገኘት ተመልክተዋል፡፡

የሲየንግ አፕ የግድብን ጥናትና ዲዛይን እንዲሁም ግንባታ ያካሄደው የኮሪያ ገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን የጄጁ ሪጂንም ስለግድቡ አስፈላጊውን ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ግድቡ 1 ነጥብ 25 ሚሊየን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን፥ 400 ሄክታር እንደሚያለማ እና በ62 ነጥብ 25 ቢሊየን የኮሪያ ዎን ወጪ እንደተገነባ ተጠቅሷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በተደረገላቸው አቀባበል እንዲሁም በቢሮና በግድቡ ቦታ በተሰጣቸው ገለጻ ልምድ ማግኘት እንደቻሉ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡