አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን ፕሬዚዳንትነት የሚመራው የቡድን 20 ‘ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ (ሲደብሊውኤ)’ ጉባኤ በአፍሪካ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት ዓላማ መሰነቁ ተገልጿል፡፡
ሲደብሊውኤ ጉባኤ በጀርመን በርሊን በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ቡድን 20 በሲደብሊውኤ ውስጥ ከአፍሪካ አጋሮች ጋር ተሃድሶ ተኮር በሆኑ ጉዳዮች እና በጋራ ግብ ላይ በቅርበት እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡
በዚህም በአፍሪካ ሀገሮች ውስጥ ያለውን ምጣኔ ሀብታዊ ሁኔታ በማሻሻል ብዙ የውጭ (የግል) ኢንቨስትመንት ወደ ሀገራቱ እንዲጎርፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትም ተጠቁሟል።
የጉባኤው ተሳታፊ ሀገሮች በዓለም ባንክ፣ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና በአፍሪካ ልማት ባንክ እንደሚደገፉም ነው የተመላከተው።
ይህም ሁሉንም ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት የሚጠቅም ልዩ የባለብዙ ወገን አጋርነት ይፈጥራል ተብሏል።
ሲደብሊውኤ አሁን በቡድን 20 እና በአፍሪካ አጋሮች መካከል እንደ ቁልፍ የትብብር ሥርዓት መቋቁሙ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም እየጨመረ በመጣው የብዝሃ-ዋልታ ዓለም ውስጥ የአፍሪካን ጠቃሚ ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያንፀባረቀ መሆኑም ተመላክቷል።
የቡድን 20 አባል ሀገራት መሪዎች እና መንግስታት ለአፍሪካ በቅርቡ በፈረንጆቹ ጥቅምት 9 እና 10 ቀን 2023 በኒው ዴልሂ ባደረጉት ስብሰባ ያሳዩትን ድጋፍ ዳግም በዚህ መድረክ እንደሚያረጋግጡም ተጠቁሟል።
የቡድን 20 የገንዘብ ሚኒስትሮች የሥራ ሂደት እና የአፍሪካ አጋሮች እንዲሁም የቡድን 20 አባላት በዓመት ለበርካታ ጊዜያት ከፍ ባለ ደረጃ ስለ አፍሪካ ሀገራት እድገት የሚወያዩበትን መድረክ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ጀርመን የቡድን 20 የአፍሪካ አማካሪ ቡድንን እንደምትመራ መገለጹን ዚስዴይ ላይቭ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!