አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ”G20 Compact with Africa (CwA)” ጉባኤ አስቀድሞ ከጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ሁለቱ ወገኖች በጋራ ትብብር መስኮች፣ በሀገር ውስጥ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የጀርመኑ መራሄ መንግስት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር መገናኘታቸው ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!